የታቀዱ

 • October 21, 2020
 • admin
 • Comment: 0

ትልማ በትምህርትና ጤና ዘርፎች የ3 ዓመት ስትራቴጂክ እቅድ በመንደፍ ልትፈፅም
የያዘቸቸው ፕሮጀክቶች
• የ30 ተጨማሪ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ግንባታ፣
• በ12 በከንቲባ የሚተዳደሩ ትላልቅ የትግራይ ከተሞች ውስጥ 12 አዳሪ ያልሆኑ ልዩ ሁለተኛ
ደረጃ ትምህርተ ቤቶች መገንባት
• በተለያዩ ወረዳዎች ባሉት ሁለተኛና መሰናዶ ትምህርት ቤቶች ውስጥ 16 የሳይንስና
ቴክኖሎጅን ማእኸላት ግምባታ፣
• በሁሉም የትግራይ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርተ ቤቶች ኦፍላይን ዲጂታል ላይብረሪ (offline
digital library) ጨምሮ ቨርቿል ኮምፑተር ማእከላትን ማቋቋም፣
• ተጨማሪ 10 የ“ኦ” ክፍሎች ግምባታ
• ከፕሮፉቸሮ ጋር በመተባበር በ200 ሙሉ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የቋንቋ እና ሳይንስ
ዲጂታል ትምህርት መጀመር፣
• 3,072 የዳስ ማስተማርያ ክፍሎች ወደ መደበኛ ክፍል መለወጥ፣
• በ2‚213 ትምህርት ቤቶች በሚስፋፋው ሶፍት ፕሮግራም በኩል ተጋሩ ህፃናት ትክክለኛው
የትግራይን ማንነት፣ ክብር፣ ታሪክና ፀጋዎችን ኣውቀው እንዲያድጉና ህዝባቸውንና
ኣገራቸውን የሚወዱ ሆነው እንዲያድጉ የሚያግዙ ስራዎችን ማከናወን፣
• የቓላሚኖ ልዩ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ዓመታዊ ተማሪዎችን የመቀበል ዓቅም ከ581
ወደ 800 ከፍ የሚል ሲሆን በአራት ምዕራፎች በሚከናወኑ የኣገልግሎት መስጫ ማስፋፋት
ስራዎች ወደ 1000 ከፍ እንዲል ማድረግ፣
• የቓላሚኖ ልዩ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የመማርና ማስተማር ሂደት በማጠናከር
የሳይንስና ቴክኖሎጂ ትምህርት የልህቀት ማእከል ሆኖ እንዲቀጥል ማድረግ፣
• በ197 ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የኣይሲቲ ማእከላት እንዲቋቋሙ ማድረግ፣
• በሁሉም የትግራይ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርተ ቤቶች ውስጥ ልዩ ክፍል ፕሮግራም/honor
Class Program በማስፋፋት ጎበዝ ተማሪዎች ለዩንቨርሲቲ የሚያዘጋጃቸው ትምህርታዊ

 • ድጋፍ ከማግኘት በዘለለ ዓቅማቸውን የሚያሳድጉበት በዩኒቨርስቲ መምህራን የመማር ዕድል
  እንዲያገኙ ማድረግ፣
  • በመላው ትግራይ 30 አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች መገንባት፣
  • ጎበዝ ተማሪዎችን ከነሱ በጣም በሚበልጡ ሌሎች ተማሪዎች እና ከዩኒቨርሲቲ መምህራን
  ጋር በመተባበር በያንዳንዱ ትምህርት ቤት ማለትም በ265ቱ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት
  ቤቶች ውስጥ አንድ የዩኒቨርሲቲ ኣስተማሪ የሚመራውና 10 ተማሪዎች የሚሳተፉበት
  በድምር 2,915 ተማሪዎችና ኣስተማሪዎች ነፃ ሃገራዊ የትምህርት አገልግሎት እንዲሰጡ
  ማድረግ፣
  • ትግራይ ውስጥ ከሚገኙት ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ጋር በመተባበር ሁለተኛ ደረጃ
  ትምህርት ቤቶች ውስጥ ለሚገኙ ኣስተማሪዎች በኢንፎርሜሽን ኮምዩኒኬሽን ቴክኖሎጂ
  ዙርያ አጭር ስልጠና መስጠት፣
  • በሚቀጥሉት 5 ዓመታት ከተለያዩ አጋሮች እና የሚመለከታቸው አካላት በአስፈላጊነቱና
  ተዛማጅ ጉዳዮች ዙርያ በመወያየት በአለም ደረጃ ካሉት ዩኒቨርሲቲዎች ጋር ተወዳዳሪ የሆነ
  የትግራይ ስቴት ዩኒቨርሲቲ (Tigrai State University) በመመስረት የትግራይን ጥቅም
  ሊያረጋግጡ የሚችሉ የላቀ እውቀት ያላቸው ተማሪዎች ለማፍራት ትኩረት ሰጥቶ
  መስራት፣
  • 7 ተጨማሪ ጤና ጣብያዎች መገንባት፤
  • 10 ተጨማሪ የጤና ኬላዎች መስራት፤
  • የ2 መካከለኛ ሆስፒታሎች ግንባታ ማጠናቀቅ እና የጤና አገልግሎት ስርዓቶች የማዘመን
  ስራዎች፣
  • ከ25 ሚልየን ብር በላይ ዋጋ ያላቸው የሕክምና መሳርያዎች ከውጭ አገራት ማስገባት፣
  • የውጭና ያገር ውስጥ በጎ ፈቃደኛ የህክምና ባለሙያዎች ሙያዊ አገልግሎት እንዲሰጡና
  እውቀታቸውና ልምዳቸውን በክልሉ ውስጥ ለሚገኙ ባለሙያዎች እንዲያካፍሉ መጋበዝ፣