ስለ ትልማ

የትልማ ኣጠቃላይ መረጃ

የትግራይ ልማት ማህበር ነሓሴ 1981 ዓ.ም በዋሽንግተን ዲሲ በኣባሎቿ የተመሰረተችና
ለትርፍ ያልተቋቅመች ድርጅት ናት። በኢትዮጵያ የሲቪል ህግ ኣንቀፅ 404 እና ሌሎች
ኣዋጆች መሰረት የተመዘገበች ህጋዊ ማህበር ስትሆን ግንቦት 1991 እ.ኤ.ኣ ዋና ፅህፈት ቤቷ
ወደ ትግራይ ክልል መቐለ ከተማ በማዘዋወር እነሆ የልማት ስራዎችን በማከናወን ላይ
ትገኛለች።
ትልማ በኣዋጅ ቁጥር 621/2009 ዓንቀፅ 112(2) የምዝገባ ቁጥር 0462 መሰረት በኢትዮጵያ
ፌደራላዊ ዲሞክራስያዊ ሪፓብሊክ (ኢፌዲሪ) የፍትህ ሚኒስቴርና የበጎ ኣድራጎት ኤጀንሲና
ማህበራት በኩል ህጋዊ ሰውነት ያገኘች ከግብር ነፃ የሆነች ድርጅት ስትሆን በማሕበረሰብ ተኮር
ልማት ላይ በመሳተፍ የያዘቻቸውን ዓላማዎች ለማሳካት እስከ ገበሬ ማህበር ድረስ የሚዘልቁ
ስራዎችን እየተገበረች ትገኛለች።
በዚህ ወቅት የትግራይ ልማት ማህበር ከተለያዩ የሕ/ሰብ ክፍሎች ማለትም ተማሪዎች፣
የመንግስት ሰራሕተኞች ፣ የንግድ ማሕበረሰብ ፣ የከተማና ገጠር ኗሪዎች ባጠቃላይ ከ1.3
ሚልየን በላይ ኣባላት ኣቅፋ በመንቀሳቀስ ላይ ነች።

የትግራይ ልማት ማህበር ከኣባላት፣ ከመንግስትና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች የሚገኝ
ድጋፍ ፣ ከማሕበሩ የሚገኙ የኢንቨስትመንት ስራዎች እንዲሁም ሌሎች የገቢ ምንጮች
በብቃት በመስብሰብና ንቁ የሕብረተሰብ ተሳትፎ ያረጋገጠና በህዝብ ፍላጎት ላይ የተመሰረተ
በመንግስት ተደራሽ ያልሆኑ መሰረታዊ የልማት ጥያቄዎች ትምህርት፣ ጤና፣ስራ ኣጥነትን
መቀነስና የክልላችንን ቋንቋና ባህልን ማዳበር የመሳሰሉትን ስራዎች በመተግበር የትግራይን
ህዝብ ኑሮ ለማሻሻል ትሰራለች።

ከድህነት እና ኋላቀርነት ነፃ የሆነች ትግራይን ማየት።

  • ግልፅነት
  • ተሓታትነት
  • ኣሳታፋይነት
  • ወለንታውነት

የትልማ ዋና ዓላማ የሕብረተስብ ንሮ ወደተሻለ ደረጃ ልማድረስ በሶው ሃብት ትኩረት ያደረገ ስራ መስራት እና የጤና ኣገልግሎት ወደ ተሻለ ደርጃ ማድረስ ነው።